በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1/2016 አንቀጽ 59 ንኡስ አንቀጽ 3 መሰረት ከአስቸካይ ጉዳዮች ውጪ የክልሉ ፍርድ ቤቶች መደበኛ የስራ ጊዜ ከነሃሴ 01 ቀን እስከ መስከረም 30 ቀን ድረስ ዝግ ሆነዉ የሚቆዩ መሆኑንና ዓላማዉም ዓመቱን ሙሉ እጅግ ከባድ በሆነ ውጥረት በብዙ ጫና ሥራ ላይ የቆዩ ዳኞች እና ባለሙያዎች በቂ እረፍት በማግኘት በታደሰ መንፈስ ሥራቸውን መቀጠል እንዲችሉ ማስቻል መሆኑን ይደነግጋል፡፡
በዚህም መሠረት የወራቤ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከነሃሴ 1/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ወራት በከፊል ዝግ ሆኖ የሚቆይ መሆኑን ለከተማ አስተዳደሩ ተገልጋይ ማህበረሰብ እንገልፃለን።
ፍርድ ቤቱ በከፊል ዝግ በሚሆንበት ጊዜ የዜጎች ፍትሕ የማግኘት መብት እንዳይጣስና ጊዜ የማይሰጣቸው አስቸኳይ የሕግ ጉዳዮችን ማየት አስፈላጊ በመሆኑ በከፊል ዝግ ወቅት የሚታዩ ጉዳዮች የሚከተሉት ብቻ ናቸዉ።
–> በወንጀል ጉዳይ፦
የዋስትና ክርክር፤
የጊዜ ቀጠሮ፤
የብርበራ ትዕዛዝ፤
የመያዣ ትዕዛዝ፤
አካል ነፃ ማውጣት ጥያቄ፤
አመክሮ፤
ቅጣት ይደመርልኝ ጥያቄ…
–> በፍትሐብሔር ጉዳይ፦
የቀለብ ክርክር፤
የሥራ ክርክርና የደመወዝ ጥያቄ፤
በተከራካሪ ወገኖች ስምምነት የተሰጡ ፍርዶች አፈፃፀም በሚመለከት
ተከራካሪ ወገኞች ስምምነት መሠረት ፍርድ እንዲሰጥ ወይም እንዲመዘገብ የሚቀርብ አቤቱታ ሆኖ ሌሎች አፈፃፀም ጉዳዮች ታግዶ የሚቆዩ ሲሆን በፍትሐብሄርም ሆነ ወንጀል ጉዳዮች ፋይል መክፈት የሚሰራ ይሆናል።
የወራቤ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት




Leave a Reply