የሴቶች ልማት ህብረት ስትሪንግ ኮሚቴ እና የፆታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት አስወጋጅ ግብረ ሀይል የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የንቅናቄ ተግባራት ግምገማ እንዲሁም የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የምክክር መድረክ አካሄደ!

የወራቤ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት “የሴቶች አቅምና ንቁ ተሳትፎ ለዘላቂ ሰላምና ብልጽግና” በሚል ሀሳብ የሴቶች ልማት ህብረት ስትሪንግ ኮሚቴ እና የፆታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት አስወጋጅ ግብረ-ሀይል የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና በንቅናቄ የሚመሩ ተግባራት ግምገማ እንዲሁም የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በዕለቱም በልማት ህብረቱ በ2018 ዓ.ም የተከናወኑ ተግባራት እና የቀጣይ ዕቅድ ቀርቦ ጥልቅ ዉይይት ተደርጎበታል።

መድረኩን የመሩት የወራቤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ነስሬ አማን፡ በሁሉም መስክ ሴቶችን ያሳተፈ ተግባር በመፈፀም እና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት እኮኖሚያዊ አቅማቸዉን ማደግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ባለፈዉ ዓመት ሴቶችን በልማት ህብረት ከማደራጀት ጀምሮ ሴቶች በእኮኖሚ እራሳቸዉን እንዲችሉ የተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ መሆናቸውን ያነሱት አቶ ነስሬ የልማት አደረጃጀቶችን ይበልጥ በማጠናከር የሚፈለገውን ዉጤት ማምጣት ይገባል ።

ሴቶች በማህበራዊ በእኮኖሚያና በፖለቲካዊ ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በማድረግ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ሃላፊዉ አስገንዝበዋል።

አቶ ነስሬ አማን አያይዘዉም የሴቶች ልማት ህብረትን በትክክል ተግባራዊ በማድረግ እና ወደ ልማት በመቀየር በሴቷ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ተጨባጭ ለዉጥ ማምጣት ይገባል።

የከተማ አስተዳደሩ ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ለይላ ጀማል በበኩላቸው እንደ ከተማ አስተዳደር የሴቶችን እኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን በመግለጽ በቀጣይም በሂደቱ ያጋጠሙ ጉድለቶችን በማረም የተሻለ ስራ መስራት ይገባል።

የሴቶችን ተጠቃሚነት እና ተሳትፎ ለማጎልበት ዕቅድ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ያነሱት ሃላፊዋ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸምም በጋራ በመገምገም የቀጣይ ተግባራት ላይ መግባባት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

ከልመና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት የፆታዊ ጥቃት እና ሌሎችንም በሴቶች ላይ የሚደርሱ ስነ-ልቦናዊ እና አካላዊ ጥቃቶችን በመከላከል ሂደት የሀይማኖት አባቶችና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች በሃላፊነት መስራት እንዳለባቸዉ ወ/ሮ ላይላ አሳስበዋል።

በሴቶች ላይ የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶችን በመከላከል ረገድ ትምህርት ቤቶች የሀይማኖት ተቋማት ወላጆች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።

ሴቶች አምራች እንዲሆኑና በዘላቂነት ከችግር እንዲላቀቁ ለማድረግ በተለያዩ ዘርፎች በማሰማራት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅንጅት መስራት ይገባል ተብሏል።

ሴቶችን በተመረጡ የንግድ ዘርፎች እንዲሰማሩ በማድረግና በዘላቂነት በመደገፍ የተረጂነት እና የልመና አስተሳሰብን ማስቀረት እንደሚገባ ተመላክቷል።

በመጨረሻም ተቋሙ በቀጣይ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የግብ ስምምነት ተፈራርሟል።

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *