የወራቤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የመረጃ አያያዙን ለማዘመንና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያስችል ዘንድ አዲስ ዌብ ፖርታል አበልጽጎ በዛሬው ዕለት በይፋ ወደ ስራ አስገብቷል።

የከተማው ብልጽግና ፓርቲ የመረጃ አያያዙን በዘመናዊ መንገድ ለማደራጀት እና ሁል-አቀፍ ሥራዎችን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ያዘጋጀው አዲሱ የዌብ ፖርታል ዘርፈ-ብዙ ፋይዳ እንደሚኖረውም ነው የተገለጸው።
ሀገራችን የጀመረችውን የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በተግባር ለማሳየትና በዘርፉ ውጤታማ ለመሆን የከተማው ብልጽግና ፓርቲ በተጨባጭ እየሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

ፓርቲው ያበለጸገው አዲሱን የዌብ ፖርታል በቀላል መንገድ ኢንተርኔት ባለበት ቦታ በስልክ እና በኮምፒውተር መጠቀም የሚቻል ሲሆን የፓርቲውን ፖሊሲዎችን፣ መመሪያዎችን፣ ዘገባዎችን እና ሌሎች በርካታ መረጃዎችን የያዘ እንደሆነ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ከዚህ ቀደም የነበረውን አሰልቺ የመረጃ አያያዝን ወደ ዲጂታል ሲስተም የቀየረው ይህ የዌብ ፖርታል ስርዓት የፓርቲውን የውስጥ ስራዎች በእጥፍ የሚያቀላጥፍ፣ ጊዜና ገንዘብ የሚቆጥብ፣ የመረጃዎችን ጥራትና ደህንነት የሚያስጠብቅ ነው ተብሏል።
ዌብ ፖርታሉ በኢንቴል ሃብ ቴክኖሎጂስ የበለጸገ ሲሆን የዚሁ ቴክኖሎጂ መስራችና ባለቤት ወጣት መንሱር ሀምዛ ስለ አዲሱ ዌብ ፖርታል ሰፊ ገለጻና ማብራሪያ ሰጥቷል።

ታዲያ የፓርቲውን ስራዎች ለማዘመን የዌብ ፖርታሉን በማበልጸግ ላደረጉት አስተዋጽኦ ለኢንቴል ሃብ ቴክኖሎጂስ መስራችና ባለቤት ለወጣት መንሱር ሀምዛ የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል።




የፓርቲው ዌብ ፖርታል ሊንክ እንደሚከተለው ተመላክቷል




Leave a Reply